Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
አንድ ቀን ሁሉም ወንጌላውያን ክርስቲያኖች የሚሳተፉበት አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደሚያሳየው በብሉይ ኪዳን ዘመን መንፈስ ቅዱስ ሕይወታችንን ተቆጣጥሮት እርሱን እንድንመስል በእግዚአብሔርና በሌሎች ፍቅር ልባችን እንዲሞላ ነው ይህ ለአንተ ሕይወት እውነት ነው።
መንፈስ ቅዱስ የሥላሴ አንዱ አካል መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል መንፈስ ቅዱስ ሁሉም የአግዚአብሔር ባሕርያት ያሉት ፍጹም እግዚአብሔር ነው ነገር ግን እርሱ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ የተለየ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚከተሉትን ነገሮች ያስተምራል መንፈስ ቅዱስ እኛ ስንፈልግ በማብራትና በማጥፋት እንደምንቆጣጠረው የኤሌክትሪክ ኃይል ማንነት የሌለው አይደለም ይልቅ መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ አንድ አካል ነው ለምሳሌ መንፈስ ቅዱስ አአምሮ አለው ያስባል እርሱ ነገሮችን ማወቅ መመርመር እና ከሚያውቀው በመነሣት ውሳኔ መስጠት ይችላል መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን ማስተማር ይችላል ኛ ቆሮ ሮሜ መንፈስ ቅዱስ ስሜት ስላለው ሊያዝን ወይም ፍቅሩን ሊያሳይ ይችላል ኤፌ ቱቁ ሮሜ እንዲሁም ፈቃድ ስሳለው አንድ ነገር እንዲፈጸም የመወሰንና እንዲሆን የማድረግ ችሎታ አለው ለምሳሌ ለእያንዳንዱ አማኝ የትኛው የመንፈስ ስጦታ መሰጠት እንዳለበት የሚወስነው ከሥላሴ አካላት አንዱ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ነው ዐኛ ቆሮ ስለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደምንረዳው መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ያለው እንጂ ግዑዝ ኃይል አይደለም መንፈስ ቅዱስ ሕያውና የራሱ ማንነት ያለው መሆኑን ብዙዎቻችን የምንስማማበት ቢሆንም አንዳንድ ክርስቲያኖች እንደ ግዑዝ ኃይል የፈቀዱትን ነገር እንዲፈጽም ሊቆጣጠሩት ሲሞክሩ ይታያሉ አንዳንድ ክርስቲያኖች ድምዓቸውን ከፍ አድርገው በኢየሱስ ስም በማሰታቸው መንፈስ ቅዱስ የሚፈልጉትን እንዲያደርግ ሊያስገድዱት እንደሚችሉ ያስባሉ። ወይም በእጅ መጫን ወይም እፍ በማሰት ወዴ ሌሎች ስዎች መንፈስ ቅዱስን ማስተላለፍ እንደሚችሉ ያስባሉ እንደዚህ ያለው ተግባር መንፈስ ቅዱስ ማንነት ያለው መሆኑን ብቻ ሳይሆን መለኮት መሆኑንም ጭምር የሚዘነጋ ነው እኛ ለራሳችን ዓላማዎች ማስፈጸሚያ እንዲውል መንፈስ ቅዱስን ልንቆጣጠረው አንችልም ከዚህ ይልቅ ራላችንን ለእርሱ ልናስገዛ ይገባናል መንፈስ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር ነው «ሰማያዊ አባታችንን እንወቅ» ከሚለው በራሪ ጽሑፍ ላይ የእግዚአብሔርን ባሕርያት መግለጫዎች ይመለከቱ መንፈስ ቅዱስ «እግዚአብሔር» ተብሏል ዐኛ ቆሮ ን ከ ኛ ቆሮ የሐዋ ን ከሐፍቂ ጋር አወዳድሩ መንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ ስለሆነ የዘላለም መንፈስ ተብሎ ተጠርቷል ዕብ ብ እርሱ በሁሉ ቦታ ይገኛል መዝ እርሱ እግዚአብሔር ብቻ ሊሰ የሚችለውን ሕይወት ይሰጣል ሮሜ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲጽፉ መርቷቸዋል ኛ ጴጥ መንፈስ ቅዱስ «መንፈስ ነው ዋናው ስሙ «ቅዱስ» የሚለውን ቃል መያዙ በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ ከሌሎች መናፍስት ሁሉ የተለየ መሆኑን ለማመልከት ነው እንዲሁም እርሱ «መንፈስ» ተብሎ ተጠርቷል ሁለት ዓይነት መናፍስት አሉ እንደ መላእክትና አጋንንት ያሉ የተፈጠሩ አካላት አሉ በሌላ በኩል ያልተፈጠሩ አካላት ደግሞ አሉ እግዚአብሔር ብቻውን መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ ያልተፈጠረ መንፈስ ነው ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደ አብ ሁሉ የሚታይ አካል የለውም እኛ ልናየው ወይም ልንዳስሰው አንችልም እኛ መኖሩን የምናውቀው በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚሠራውን ሥራ በማየት ነው ዮሒ ሰዎች ከራስ ወዳድነት ወደ አፍቃሪነት ሰው ወዳድነት ሲለወጡ በዚያ መንፈስ ቅዱስ መኖሩን እናውቃለን ወይም ሰዎች ለመመስከር ድፍረት ማግኘታቸውን ስንመለከት ወዘተ የሐሞ ፉ በዚህ መንፈስ ቅዱስ መኖሩን አናውቃለን መንፈስ ቅዱስ እርሱ መንፈስ ስለሆነ በየትኛውም ስፍራ በአንድ ጊዜ ይገኛል እርሱ በሰማይና በምድር ይኖራል እርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ እንዲሁም በየትኛውም የዓለም ክፍል ይኖራል በእኔና በአንተ ልብ ውስጥ በአንድ ጊዜ ይኖራል በዚህ ምክንያት እያንዳንዳችን በመከራ ውስጥ በምናልፍባቸው ጊዜያት ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እኛ ብቻችንን ላለመሆናችን ዋስትናን ይሰጠናል የሥላሴ አንደኛው አካል እንደ መሆኑ መጠን መንፈስ ቅዱስ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር አብና ከአግዚአብሔር ወልድ ጋር እኩል ነው ሆኖም ከአነርሱ የተለየ ነው ኢየሱስ በተጠመቀበት ጊዜ እግዚአብሔር አብ ከሰማይ ተናገረ በተመሳሳይ ወቅት ኢየሱስ በወንዙ ውስጥ ቆሞ ነበር በዚያኑ ሰዓት መንፈስ ቅዱስም በኢየሱስ ላይ ወረደበት ማቴ ፁኻ ይህ አውነት በሦስት የተለያዩ ስሞች የተጠራ አንድ አምላክ ብቻ ነው ያለው የሚለውን የ«ኢየሱስ ብቻ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ውድቅ የሚያደርግ ነው እግዚአብሔር አብ ስለ ራሱ እኔ በራሴ ተደስቻለሁ ብሎ ይናገራልን። ብዙ ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ በሚያስቡበት ጊዜ በልሳናት ስለ መናገር ስጦታ ወይም ስለ ተአምራዊ ሥራዎች ማሰባቸው ነው መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ክርስቲያኖች በልሳናት እንዲናገሩ ችሎታ ይሰጣቸዋል አንዳንድ ጊዜም ተአምራትን እንዲሠሩ ያስችላቸዋል ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህ የመንፈስ ቅዱስ ዋና አገልግሎቶች መሆናቸውን አያሳየንም ለማንኛውም አንድ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ትኩረት እንዳንሰጥ መጠንቀቅ ይኖርብናል እንደዚህ ካደረግን በቡና ውስጥ ጨው በብዛት መጨመር እንደምትወድ ሴት ይመስላል ሴቲቱ በአንድ ስኒ ቡና ውስጥ በጣም ጥቂት ጨው በመጨመር ፈንታ ብዙ ጨው ትጨምራለች ጨው መጨመሩ መልካም ቢሆንም መብዛቱ ግን የቡናውን ጣዕም ያበላሸዋል ስለዚህ እኛም ለመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ሁሉ ሚዛን ካላበጀን በፍጹም ጤናማ የሆነ መንፈሳዊነት ሊኖረን አይችልም መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም የሕይወታችን ገጽታዎች ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ተሳትፎ እንዳለው ያስተምረናል መንፈስ ቅዱስ ሁሉም ነገር በሚፈጠርበት ጊዜ ተሳትፏል በዘፍጥ ላይ መንፈስ ቅዱስ በውኃዎች ሁሉ ላይ ሰፍፎ እንደነበር ተገልዷል ይህም መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ፍጥረት ወደ መኖ እንዲያመጣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመፈጸም ዝግጅት ላይ እንደነበረ ያለጥርጥር የሚያመለክት ነው መንፈስ ቅዱስ ለሁሉም ሕይወትን በመስጠትና ፍጥረት በምድር ላይ ጸንቶ እንዲቀጥል በማድረግ ተግባርም ላይ ተሳታፊ ነው መዝ ብ ኢዮብ ሓብ በታሪክ ውስጥ እንደምንመለከተው ለሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ይገልጽላቸው የነበረው መንፈስ ቅዱስ ነው መንፈስ ቅዱስ ይህን ተግባር የፈጸመው በሁለት መንገድ ነው አንደኛ መንፈስ ቅዱስ ለብዙ ነቢያት ፈቃዱን በመግለጽ ተናግሯል አንዳንዶቹ ነቢያት መንፈስ ቅዱስ የነገራቸውን በጽሑፍ አላሰፈሩም ነገር ግን ለሌሎች ሰዎች በቃል አስተላልፈዋል ለምሳሌ በለዓም በበትል ሐብ አዛሪያስ ኛ ዜና ፊ በዘመናት ያሉ ሰዎች ሁሉ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ፈቃዱ የሚናገረውን ቅዱስ ቃሉን እንዲያውቁ ይረዳቸው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ሰዎችን ቃሉን በጽሑፍ እንዲያሰፍሩ አድርጓቸዋል ይህም ምንም ስሕተት በሌለበትና ለሁልጊዜም በሚያገለግለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል ኛ ሳሙ ሚክ ማቴ የሐዋ ኛ ጢሞ ኛ ጴጥ ሁለተኛ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለልጆቹ መግለጹን ይቀጥላል ይህም አንዳንዴ በራእይ ወይም በትንቢት አማካይነት ሊሆን ይችላል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ይህንን የሚያደርገው በዋናነት የተጻፈውን ቃሉን እንድንረዳና በተግባር እንድናውለው በመርዳት ነው ኛ ቆሮ ፁዛ መንፈስ ቅዱስ በግልጽ በቃሉ ውስጥ የተናገረውን የማናነብና በተግባር የማናውለው ከሆነ በሌላ መንገዶች ለምን ይናገራል። » ከሚል ርእስ ሥር የተቀመጡትን ትንታኔዎች ተመልከት ሁለተኛ እኛ መንፈስ ቅዱስን እንድንቀበል አንዳች ነገር ማድረግ እንደሚገባን አዲስ ኪዳን አያስተምርም መጽሐፍ ቅዱስ ወደ እርሱ ለሚጸልዩ ለሚጾሙ ወይም ልዩ በሆነ መንገድ ለተቀደሱ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጥ አይናገርም ማስታወሻ በሉቃስ ሳይ ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሔር እጅግ ታላቅ በረከት የሆነው መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጣቸው እንዲለምኑ ኢየሱስ ያበረታታቸዋል ይህ ጸሎት በሐዋ ሥራ ላይ ተከታዮቹ መንፈስ ቅዱስን በተቀበሉበት ጊዜ ምላሽ አግኝቷል ስለዚህ ዛሬ መጸለይ ያለብን ጸሎት አይደለምራኑ መጸለይ የሚገባን መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ መንፈስ ቅዱስ እንዲቆጣጠረንና በውስጣችን ለእግዚአብሔር ክብር የሚያመጣ ነገር እንዲሠራ ነው እያንዳንዱ አማኝ ባመነበት ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶታል የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሰዎች እንዳደረጉት ኃጢአት እንኳን በሕይወታችን ውስጥ እያለ ኛ ቆሮ እና እንደሚነግሩን አሁንም «የእግዚአብሔር ቤተ መቅደሶች» ነን ኃጢአት በምንሠራበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አይተወንም ከዚህ ይልቅ ያዝናል ኤፌ በእኛ የመሥራት ኃይሉም ይገደባል መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ ወደ አማኙ ሕይወት ውስጥ በሚመጣበት ጊዜ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል ሀ መንፈስ ቅዱስ የአማኙን ኃጢአት አጥቦ ከእግዚአብሔር ጋር የተስተካከለ ግንኙነት እንዲኖረው ያደርጋል በኛ ቆሮ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህን ጊዜ ምን እንደሚፈጸም ለመግለጽ የተለያዩ ቃላትን ይጠቀማል ልክ ሳሙና በልብሶቻችን ላይ ያለውን እድፍ እንደሚያስወግድ መንፈስ ቅዱስ የኃጢአታችንን ቆሻሻ አጥቦ ያስወግዳል ቲቶ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ «ይቀድሰናል» የዚህ ቃል ትርጉም «መለየት» ማለት ነው በዳንንበት ጊዜ እኛ ከዓለም ተለይተናል የእግዚአብሔር ልጆች ስለምንሆን በዚህ ጊዜ የተለየን እንሆናለን ድድቃቅ እንቀበላለን ጽድቅ የሚለው ቃል ትርጉሙ በደል የለባችሁም መባል ነው ጻድቅ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር ለሠራነው ኃጢአት ሁሉ በደለኞች አይደላችሁም ብሎናል ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት የኃጢአታችንን ዋጋ ስለከፈለ ኃጢአታችን ካስከተለው ዘላለማዊ ቅጣት መዘዞች የተነሣ አሁንም እየተሠቃየን ብንሆንም ዘላለማዊ ቅጣት እንደማንቀበል እግዚአብሔር በቃሉ ነግሮናል ሮሜ ከእነዚህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች የተነሣ አማኙ ሊቀደስና ከቅዱሱ እግዚአብሔር ጋር ኅብረት ሊያደርግ ይችላል ኃጢአት በምንሠራባቸው ጊዜያት ሁሉ ያለን ኅብረት ይበላሻል ሆኖም ደኅንነታችንን አናጣም ኃጢአታችንን በምንናዝዝበት ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአታችን ሁሉ አንጽቶ ዳግም ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖረን ያደርጋል ዐበኛ ዮየዮሔሑ ለሊ መንፈስ ቅዱስ አዲስ ፍጥረት ያደርገናል እኛ ኢየሱስን ከማመናችን አስቀድሞ ከነበረን አኗኗርና ድርጊት ተለውጠናል ኛ ቆሮ ገላ ሔ መንፈስ ቅዱስ ከሰይጣን ልጅነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ለውጦናል ዮሐ ሮሜ ገላ «ዱን መ መንፈስ ቅዱስ ማኅተማችንና ዋስትናችን ነው ኛ ቆሮ ኤፌ የገዛነው መጽሐፍ የእኛ ለመሆኑ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ በላዩ ላይ ስማችንን እንደምንጽፍበት ሁሉ በውስጣችን የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ እንደ እግዚአብሔር ማኅተም ነው መንፈስ ቅዱስ እኛ የእግዚአብሔር መሆናችንን ያሳያል አንድ ላም ለመግዛት ቀብድ ለባለቤቱ ከሰጠን ያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አሟልተን እንደምንከፍል ማረጋገጫ ነው ይህንን በመሰለ ሁኔታ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በልባችን ውስጥ ማስቀመጡ ልጆቹ እንደ መሆናችን መጠን አንድ ቀን የእርሉ የክብር ህልውና ወደሚገኝበት ወደ ሰማይ እንደሚወስደን ማረጋገጫ መስጠቱ ነው ሠ መንፈስ ቅዱስ ያጠምቀንና የክርስቶስ አካል ክፍል እንድንሆን ያደርገናል ኛ ቆሮ ጳውሎስ እዚህ ላይ የሚናገረው ብዙ አማኞች ካመኑ በኋላ ስለሚፈጽሙት የውኃ ጥምቀት አይደለም ከዚህ ይልቅ ጳውሎስ እየነገረን ያለው በኢየሱስ ባመንንበት እና መንፈስ ቅዱስ ወደ ልባችን በመጣበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት አድርጎናል በማለት ነው ይህ ቤተሰብ «የክርስቶስ አካል» ተብሎም ይጠራል እዚህ ላይ ጳውሎስ አባል ስለሆነበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ መናገሩ አይደለም ወይም እኛ ስላለንበት ቤተ እምነት መናገሩ አይደለም ከዚህ ይልቅ በየትኛውም ቤተ እምነት የሚገኙት እውነተኛ ክርስቲያኖች አሁን አንድ አካል መሆናቸውን ነው የሚናገረው ሁሉም አማኞች የእግዚአብሔር ልጆች ከሆኑ እኛም የዚህ ቤተሰብ አባል ነን ማለት ነው ይህ የአማኞች ኅብረት «የክርስቶስ አካል» ተብሎ ይጠራል ምክንያቱም ኢየሱስ አገልግሎቱን በዚህ ምድር ላይ የሚቀጥለው በአማኞች አማካይነት ነው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ምሪትንና አቅጣጫን ለቤተ ክርስቲያን የሚያሳየው «ራስ» እርሱ ነው ኤፌ ቱ እኛ አሁን የእርሱ እግሮች እጆችና አፍ ነን በእርሱ ምትክ አማኞችንና የተቀረውን ዓለም እናገለግላለን እንደ እርሱ እግሮች ወንጌሉን በዓለም ሁሉ ይዘን እንዞራለን እንደ እርሱ አንደበት ደኅንነትን የሚያመጣውን የእውነትን ቃል ሰዎችን በእምነታቸው እንዲያድጉ ብዙ አማኞች እምነታቸውን በክርስቶስ ላይ ያደረጉ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የማያገለግሉ መኖራቸው የሚያሳዝን አጋጣሚ ነው የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባል ሆነዋል በየሳምንቱ ለመዘመርና የእግዚአብሔርን ቃል ሰመስማት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣሉ ነገር ግን እንደ ኢየሱስ አፍ ወይም እጆች ወይም እግሮች ተገቢውን ተግባር አያከናውኑም መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ከሚኖርባቸው ምክንያቶች አንዱ እኛን በመጠቀም ሌሎችን ለማገልገል ነው አንተ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ነህን። አንዳንድ ጊዜ ስዎች የማይስማሙት አንዱን ቃል በተለያየ መንገድ ስለሚረዱት ነው ለምሳሌ አንድ ስው ራእይ የሚለውን ቃል የወደፊት ተስፋዎችን ወይም ሕልሞችን ለማመልከት ይጠቀምበታል ሌላው ሰው ይህንኑ ቃል ስንተኛ ስለሚታየን ሕልም ወይም እግዚአብሔር ስሰ ሰጠው መልእክት ለማመልከት ይጠቀምበታል እነዚህ ሁለት ሰዎች ለቃሉ ተመሳሳይ የሆነ ግንዛቤ ከሌላቸው በስተቀር በሚነጋገሩበት ጊዜ ግራ መጋባትና አንዱ ሌላኛውን በተሳሳተ መንገድ መረዳት ይጀምራል አብዛኛውን ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆን ወይም በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ወይም በመንፈስ ቅዱስ መሞላት የሚሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት በምንጠቀምበት ጊዜ ተመሳሳይ የሆነ ችግር ይከሰታል አንዳችን የሌላውን በአግባቡ መረዳት እንድንችል በምንነጋገርበት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ቃላት ወይም ሐረጎች በምን መልኩ እንደተጠቀመባቸው እና የመንፈስ ቅዱስን አገልግሎት እንደገለጸ ማወቁ በጣም ጠቃሚ ነው የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ከመገንዘብ አንጻር ልዩነቶች ካሉን ችግሩ ቃላትን ካለመረዳት የተነሣ አይደለም ችግሩ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እያንዳንዱ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሉት የሚያስተምረውን ከተረዳንበት መንገድ የተነሣ ነው ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ግራ የሚጋቡባቸው ሦስት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች አሉ የመንፈስ ቅዱስ በሰዎች ውስጥ የማደር አገልግሎት ቀደም ብለን በግልጽ እንዳየነው መንፈስ ትዱስ በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ ይኖራል ዱ ውስጥ ይኖ ዮሒ ሮሜ ኛ ቆሮ በአዳኛ ችን በኢየሱስ ላይ መታመን ከምንጀምርበት ጊዜ አንሥቶ በውስጣችን ለመኖር ይመጣል የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ይህ መንፈስ ት ሎት ነው ህ አገልግሎት አንድ ጊዜ ከተፈጸመ በኋላ የሚደጋገም አይደለም ኛ ቆሮ አዳዲስ ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ መጸለይና መጾም ያስፈልጋቸዋል ብለው የሚያስተምሩ ክርስቲያኖች አሉ እነርሱ እንደሚሉት የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአነዚህ ሰዎች ላይ መጥቶ በልሳናት እንዲናገሩ ያስችላቸዋል እነርሱ ይህንን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ብለው ይጠሩታል አዲስ ኪዳን ግን ይህን የሚያስተምር አይመስልም ሀሁ ኢየሱስ ሰዎችን በመንፈስ ቅዱስ እንደሚያጠምቅ መጥምቁ ዮሐንስ ተነበየ ማር በዚህ ጊዜ ይህንን ጥምቀት የሚቀበሉት ሰዎች ማድረግ ስለሚገባቸው አንዳች የተለየ ነገር ወይም መንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው ጥቂት አማኞችን ብቻ ስለመሆኑ ምንም አልተጠቀሰም እንዲሁም የዚህ ጥምቀት ማረጋገጫ ሆኖ ስለሚከተለው ነገር ምንም አልጠቀሰም ለ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከመመለሱ ከማረጉ አስቀድሞ በቅርቡ በመንፈስ ቅዱስ እንደሚያጠምቃቸው ለሐዋርያት ነግሯቸዋል የሐዋ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆንና መጠመቅ በሐዋርያት ሥራ በሁሉም ሐዋርያት ሕይወት ውስጥ ተፈጽሟል ለስጦታው ምንም ቅድመሁኔታ አላስፈለገም ሒ ሴኔጥሮስ ለተስበሰቡት አይሁዳውያን በሰበከበት ወቅት በኢየሱስ ያመኑ ሁሉ መንፈስ ቅዱስን እንደሚቀበሉ ቃል ገብቶላቸዋል በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው አልተናገረም መ በኛ ቆሮ ላይ ደካሞችና ኃጢአተኞች የነበሩትን የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አማኞች «ሁሉም» በመንፈስ ቅዱስ መጠመቃቸውን ተናግሯል ሠ አዲስ ኪዳንን በጥንቃቄ ያጠናን እንደሆነ አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ ይችሉ ዘንድ እግዚአብሔር ምንም ዓይነት ትእዛዝ ሲሰጥ አናይም እግዚአብሔር አማኞች አንድ ልዩ በረከትን እንድንቀበል ማድረግ ያለብን ነገር ቢኖር ኖሮ ማድረግ የሚገባንን በትእዛዝ መልክ በሰጠን ነበር ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምንም የተስጠ ትእዛዝ የለም በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ በኢየሱስ ክርስቶስ ከማመን ውጭ የተዘረዘረ ቅድመሁኔታ የለም ይልቅ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቃቸው እንደ ስጦታ በነፃ መሆኑን ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል የሐዋ ፋ ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አገልግሎት እምነታችንን በክርስቶስ ላይ ካደረግንበት ከመጀመሪያው ጊዜ አንሥቶ በእውነተኛ አማኞች ሁሉ ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራው ነገር መሆኑን ማመን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይመስላል እኛ በመንፈስ ቅዱስ በምንጠመቅበት ጊዜ የሚፈጸመው ምንድን ነው። ምን ማድረግ እንዳለብን በድጋሚ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠን ጥቂት መመሪያዎችን ብቻ ነው በእግዚአብሔር የተሰጠ ትእዛዝ እንደ መሆኑ መጠን በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት አንዳች ነገር ማድረግ እንደሚገባን ግልጽ ነው ሁላችንም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተን በእርሱ ምሪትና ኃይል ሥር እንድንኖር የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑ በጣም ግልጽ ነገር ነው እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ በማንሞላበት ጊዜ ችግሩ የእግዚአብሔር ሳይሆን የራሳችን መሆኑ በጣም ግልጽ ነው የእርሱ ፍላጎት እኛ በመንፈስ ቅዱስ መሞላታችን ነው ስለዚህ ነው በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ ያዘዘን የሚከተሉት ነገሮች በመንፈስ ትዱስ እንድንሞላ ልናደርጋቸው የሚገቡን ነገሮች ው አንደኛ መጸለይ እንችላለን መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ መጸለይ ያስፈልጋችኋል ብሎ በቀጥታ ባይናገርም መጸለይ እንደሚገባን ምንም ጥርጥር የለውም በተለይ በጣም የሚያስቸግሩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ወይም ኃጢአት እንድናደርግ ስንፈተን ወይም የስብከት ወይም የማስተማር አገልግሎት በሚኖረን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ባልተሰመደ ኃይል እንዲሞላን ልንጸልይ ይገባል ይህም እርሱ በሚፈልገው ዓይነት መኖርና ማገልገል እንችል ዘንድ ነው በየዘመኑ ታሪክ ውስጥ እንደታየው የሰዎችን ሕይወት ሥር ነቀል በሆነ መንገድ የሚለውጥ ይህ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚከሰትበት ወቅት የታወቀ ነው ይኸውም ሰዎች ከኃጢአታቸው ንስሐ ከገቡና እግዚአብሔር እንዲለውጣቸውና ለክብሩ እንዲጠቀምባቸው በሕይወታቸው ጥልቅ ፍላጎት ካደረባቸው በኋላ ነበረ ይህም እግዚአብሔር «እናንተ ትችሹኛላችሁ በፍጹም ልባችሁም ካሻችሁኝ ታገኙኛ ላችሁ» ኤር ባለው መሠረት ነው ሁለተኛ በሕይወታችን የሚታየው ሁኔታ መንፈስ ቅዱስ ሊሞላን ፍላጎት እንዲያድርበት የሚፈቅድ ለመሆኑ አርግጠኛ መሆን ይኖርብናል በኤፌ ፋ ሐዋርያው ጳውሎስ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተያያዙ ሁለት ትእዛዛትን ይሰጠናል የመጀመሪያው «መንፈስ ቅዱስን አታሳዝኑ ኤፌ የሚል ሲሆን ሁለተኛው መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ» ኤፌ የሚል ነው መንፈስ ቅዱስን የሚያሳዝነው ምን እንደሆነና በመንፈስ እንዳንሞላ ዕንቅፋት የሚፈጥርብን ምን እንደሆነ ለማወቅ ዐውደ ምንባቡን ኤፌ ቁ ማጥናት ይጠበቅብናል በኤፌሶን ምዕራፍ ላይ አማኞች ከሕይወታችን ውስጥ ኃጢአትን ማስወገድ እንደሚገባን ይነግረናል እነዚህም ዝሙት መዋሸት ሌብነት መለያየት ሐሜት ጥል የመሳሰሉት ናቸው መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ስለሆነ በመንፈሱ የሚሞላቸው ሰዎች ከሕይወታቸው ኃጢአትን ያስወገዱትን ነው እንዲሁም ጳውሎስ አማኙ በሕይወቱ እግዚአብሔርን የመምስል ባሕርያትን እንዲጨምር ያሳስባል እኛ ከሰዎች ጋር በሰላም እንድንኖር ያስፈልጋል እውነትን ልንናገር ፍቅርንና ርኅራጌን ልናሳይ የጽድቅ ሕይወት ልንኖር ጠንክረን ልንሠራ የበደሉንን ይቅር ልንል ወዘተ ይገባናል እነዚህን ባሕርያት በራሳችን ጥንካሬ ልናዳብራቸው የማንችልና የመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ የሚያስፈልገን ቢሆንም እነዚህን በሕይወታችን በተግባር ላይ ለማዋል መወሰን ይኖርብናል የእኛ ዋና ጸሉት በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ በሩን የሚከፍትልን የጽድቅና የቅድስና ሕይወት እንድንቀዳጅ እግዚአብሔር እንዲረዳን ሊሆን ይገባል ኃጢአታችንን በንስሐ በማስወገድ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ጠንክረን እየሠራን ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ስንኖር ያን ጊዜ እንደ እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ እንሞላለን የሐዋ ሦስተኛ በመካከላችን መንፈስ ቅዱስ እየሠራ ያለውን ሥራ የሚያደናቅፍ ተግባር መፈጸም አይገባንም በኛ ተሲ ሳይ መንፈስን አታጥፉ» ተብለናል በዙሪያው ከሚገኙት ጥቅሶች እንደምንረዳው የመንፈስን እሳት የምናጠፋው እርሱ በመካከላችን እየሠራ ያለውን ነገር በምንቃወምበት ጊዜ ነው ለምሳሌ ያህል መንፈስ ቅዱስ በይፋ መሪ ባልሆነ ሰው አንድን አዲስ ነገር ሊሠራ በሚፈልግበት ጊዜ ነገር ግን መሪዎች ያንን አገልግሎት ሲያደናቅፉ ያን ጊዜ እሳቱን አጠፉ ማለት ነው እነዚህ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ በሚፈልገው ሰው ሊፈጽም የፈለገውን ነገር እንዳያደርግ እያደናቀፉት ነው ማለት ነው ወይም እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን መልእክት ወደ አንድ ሰው ልብ አስተላልፎ ሰዎች መልእክቱን ለመስማት በማይፈልጉበት ጊዜ ያኔ የመንፈስ ቅዱስን እሳት አዳፈኑት ማለት ነው ይህንንም በማድረጋቸው እኛ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ አናዳምጥም ማለታቸው ነው። ጳውሎስ የሚመልስላቸው መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች የሚሰጣቸው ብዙ ስጦታዎች አሉ በልሳናት መናገር ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ብቻ ነው በማለት ነው መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ እንደምናየው በተለያዩ መንገዶች ሠርቷል እያንዳንዱ አሠራር የተለየ ነበር ይህ የሚያሳየው በአማኙ ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ለመኖሩ ማረጋገጫው አንድ የተወስነ መንገድ ብቻ ሊሆን እንደማይችል ነውፎ ጥንቃቄ የተሞላበት የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ጥናት የሚከተሉትን ያሳያል ሀ የሐዋ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ በደቀ መዛሙርቱ ላይ በመጣበት ጊዜ ራታም እኩል የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ተቀብለዋል እንዲሁም ቻታም በልሳናት ተናግረዋል እነዚህ ልሳናት የሰው ቋንቋዎች እና ደቀ መዛሙርቱ የማያውቋቸው ሌሎች አድማጮቻቸው ግን የሚያውቋቸው ነበሩ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል እንደ ጾም ወይም ጸሎት ያሉ ልዩ ነገሮችን ያደርጉ እንደነበረ የሚገልጽ አንድም ነገር አናይም እንዲሁም ይህ ልዩ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ አመጣጥ ሁልጊዜ በማናቸውም ክርስቲያኖች ላይ የሚከተለው የአመጣጥ መንገድ ለመሆኑ ምንም ፍንጭ አይታይም በዚህ ፈንታ ይህ ልዩ ልምምድ የቤተ ክርስቲያን ምሥረታ እና በሁሉም ክርስቲያኖች ላይ የመንፈስ ቅዱስን መምጣት ለማመልከት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አንድ ጊዜ የተፈጸመ ይመስላል ይህ ለክርስትና ሕይወት መደበኛና ለሁልጊዜ የሚሆን ምሳሌ ቢሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ታላቅ ነፋስና የእሳት ልሳናትን እንጠብቅ ነበር ይህ ግን ሊሆን አይችልም ይህ አይሁዶች ከዳኑ በኋላ መንፈስ ቅዱስ የመጣበት የመጨረሻው ክስተት ነው ከጴጥሮስ ስብከት የሐዋ እና ከጳውሎስ የመጨረሻ ትምህርት ሮሜ እንደምንመለከተው ከዚህም በኋላ መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ የሚታዩት ሰመጀመሪያ ጊዜ በክርስቶስ በሚያምኑበት ወቅት ብቻ ነበር ለሌ የሐዋ ጴጥሮስ ያዳምጡት የነበሩት አይሁድ እነርሱም ካመኑ ከደቀ መዛሙርቱ እኩል ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደሚችሉ ቃል ገብቶላቸዋል ሆኖም ለመንፈስ ቅዱስ መጸለይ እንደሚገባቸው አልተናገረም እንደዚሁም መንፈስ ቅዱስን በሚቀበሉበት ጊዜ ሁላቸውንም በልሳናት ትናገራላችሁ አላለም ወይም ሐዋርያት አጃቸውን ጭነው መንፈስ ቅዱስንና በልሳናት መናገርን እንዳስተላለፉ የተጻፈ ነገር የለም በታሪኩ ውስጥ እንደተገለጸው አይሁዳውያን እንዳመኑ ወዲያውኑ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለዋል ሔ የሐዋ ፋ በሁሉም የሰማሪያ አማኞች ላይ እንዳመኑ ወዲያውኑ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው ይሁንና በመንፈስ የተሞላው ታዋቂው ወንጌላዊ የእግዚአብሔር ሰው ፊልጳስ ለሳምራውያን መንፈስ ቅዱስን ሊሰጣቸው ኣልቻለም ነበር ለዚህም ምክንያቱ ኢየሱስ አዲስ ማኅበረሰብን ወደ ቤተ ክርስቲያን የማምጣቱን መብት የሰጠው ለጴጥሮስ ስለነበር ነው ስለዚህ ጴጥሮስ መጥቶ የሳምራውያንን እምነት እስኪያረጋግጥ ድረስ እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን መምጣት አዘገየው እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን መምጣት ያዘገየው ሳምራውያን በአይሁድ የተጠሉ ሕዝቦች ቢሆኑም እንኳ በኢየሱስ ክርስቶስ እስካመኑ ድረስ ከአይሁድ እኩል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው መሆኑን ለማመልከት ጭምር ነው እግዚአብሔር ለአይሁድ መንፈስ ቅዱስን በሰጠበት በዚያው መንገድ ለሳምራውያንም ሰጥቶአቸዋል ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአይሁድና በሳምራውያን መካከል ምንም ልዩነት መኖር የለበትም አይሁዳውያን አማኞች ከሳምራውያን የተሻልን ነን ብለው እንዲያስቡ የሚያስችላቸው ምንም ምክንያት አልነበረም እግዚአብሔር ጴጥሮስን በመጠቀም የራሳቸው ሥርዓተ አምልኮ የነበራቸውን ሳምራውያን ከአይሁድ ነፃ የወጣ የአምልኮ መስመር ሊኖራቸው እንደማይችል አስተምሯቸዋል ሳምራውያን ከአይሁዳውያኑ ሐዋርያት ሥልጣን ሥር መሆን እና በኢየሩሳሌም ለምትገኘው እናት ቤተ ክርስቲያን መገዛት ነበረባቸው አይሁዳውያኑ በግለሰቦች ላይ እጅን በመጫን ቡራኬን የሚያስተላልፉበት ተግባር እዚህ ላይም የመንፈስ ቅዱስን መምጣት ለማነሣሣት ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ሲውል ይታያል ሐዋርያት የሰማሪያ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድባቸው እንዲጸጾሙና እንዲጸልዩ አልነገሯቸውም ለእኛም ቢሆን የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ማስረጃው ይህ ነው ተብሉ አልተነገረንም በልሳናት ስለመናገርም የተጠቀሰ ነገር የለም ይህ ላምራውያን በክርስቶስ ካመኑ ከጥቂት ጊዜ በቷላ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደባቸው ለመጨረሻ ጊዜ የሚናገር ክፍል ነው መ የሐዋ በቆርኖሌዎስ ቤት ተሰብስበው በነበሩ የአሕዛብ አማኞች ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ እዚህ ላይም ጴጥሮስ አዲስ ማኅበረሰብን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲያመጣ እግዚአብሔር በድጋሚ ሲጠቀምበት ይታያል ይህም በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እመሠርታለሁ ሲል ኢየሱስ ለጴጥሮስ የገባለት ተስፋ ፍጻሜ ነው ማቴ ጴጥሮስ በረከትን ለማስተላለፍ በአሕዛብ አማኞች ላይ እጁን መጫን አላስፈለገውም እንዲያውም መንፈስ ቅዱስ የወረደው ገና ጴጥሮስ ስብከቱን ሳይጨርስ አረማውያን በኢየሱስ እንዳመኑ ነበር ራታም ከአሕዛብ ወገን የመጡ አማኞች መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ በልሳናት መናገር ጀመሩፎ እንዴት በልሳናት መናገር እንደሚችሉ ግን መማር አላስፈለጋቸውም መንፈስ ቅዱስ ይወርድባቸው ክንድ መጾምና መጸለይም አላስፈለጋቸውም ከዚህ ወዲህ ሌሎች አሕዛብ ደኅንነትን ከተቀበሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንደ ልሳን ያሉ የሚታዩ ስጦታዎች ሲወርድባቸው አልታየም ቀድሞ በአይሁድ ጠላትነታቸው የሚታወቁት አሕዛብ በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ እኩል መሆናቸውን እግዚአብሔር ለአይሁድ ለማሳየት የፈለገ ይመስሳል አሕዛብ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት አይሁዳውያኑ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉበት ሁኔታ ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነው ይህ የሚያሳየን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጎሳ ሳቢያ መከፋፈል ሊኖር እንደማይገባ ነው ሠ የሐዋ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት በኢየሱስ ክርስቶስ ባመኑ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወርዶባቸዋል እስከዚህ ጊዜ ድረስ ብዙ ሰዎች መሚሑ ኢየሱስ መሆኑን ያስተምር የነበረውን መጥምቁ ዮሐንስን ይከተሉ ነበር ነገር ግን ዮሐንስ ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በፊት ሞተ በመሆኑም እነዚህ የዮሐንስ ተከታዮች ሙሉውን የወንጌል መልእክት ማለትም ኢየሱስ ስለ ኃጢአት መሞቱንና መነሣቱን አያውቁም ነበር ከዚያም ጳውሎስ ወንጌልን ከገለጸላቸው በኋላ አመኑ በዚህን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ጭኖ መንፈስ ቅዱስን ወደ እነርሱ አስተላለፈፊ ከጳውሎስ ጋር የነበሩትና ያመኑት የመጥምቁ ዮሐንስ ተከታዮች ሙታ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው በልሳናት ተናገሩ ከዚህም በቷላ በዚህ ዓይነት ያልተለመደ ሁኔታ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለመኖራቸው አልተጠቀሰም ማስታወሻ ምናልባት ይህ ታሪክ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ የተጠቀስበት ምክንያት ሁሉም የመጥምቁ ዮሐንስ ተከታዮች እውነተኛ አማኝ ለመሆን በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ላይ እምነታቸውን ማድረግ እንደሚገባቸው ለማስተማር ነው የመጥምቁ ዮሐንስን ትምህርት ብቻ መከተል በቂ አልነበረም ማስታወሻ በእነዚህ አራት ያልተለመዱ የመንፈስ ቅዱስ አመጣጦች የመንፈስ ቅዱስ ማደር የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ የመጀመሪያ ሙላት የተከናወኑት በአንድ ጊዜ ነው ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ አስደናቂ አመጣጥ በሰው ውስጥ የማደሩ የማጥመቁና የመሙላቱ ማስረጃ ነው ብሎ ማለት አይቻልም በዚህ ፈንታ መልእክቶች በእነዚህ ሦስት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ዙሪያ ምን አንደሚሉ ግልጽ መረዳት እንዲኖረን ማጥናት ያስፈልገናል ማጠቃለያ ሀ ከላይ በተመለከትናቸው ልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ የተጠቀሱት ወገኖች መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት በአንድ ጊዜ ነው መንፈስ ቅዱስን ያልተቀበለ ማንም ሰው በመካከላቸው አልነበረም ለ በአንድ ሰው ውስጥ ለማደር የመጣው መንፈስ ቅዱስ ምናልባት በልሳናት መናገርን አስከትሎ ይሆናል ነገር ግን ይህ ሁልጊዜ የግድ አስፈላጊ ነው ማለት አይደለም ሐ አንዳንድ ሰዎች ያለእጅ መጫን መንፈስ ቅዱስን እስከ ተቀበሉ ድረስ እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በልሳናት ለመናገር የግድ አስፈላጊ ያለመሆኑን ያሳያል መ ሁልጊዜ በልሳናት መናገር በቅጽበት የሚሰጥ ስጦታ እንጂ ማንም ሰው በልሳናት ለመናገር መማር አያስፈልገውወም ሠ ማንም ሰው ላይ እፍ በማለት በመነቅነቅ ወይም በመግፋት መንፈስ ቅዱስን ማስተላለፍ አይቻልም ሪ ሁሉም መንፈሳውያን ክርስቲያኖች በልሳናት አይናገሩም ሰ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የምናያቸው ትዕይንታዊ የመንፈስ ቅዱስን አመጣጦች ልዩ ልምምዶች እንጂ ሁሉም ክርስቲያኖች ዛሬም መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ሊከተሉ የሚገባቸው ምሳሌዎች አይደሉም በልሳናት መናገር ትርጉም የለሽ ቃላትን መደጋገም ሳይሆን ቋንቋ ነው አንዳንድ አማኞች ብዙና የተለያዩ ዓይነት ልሳናት መኖራቸውን ለማስተማር ይፈልጋሉ በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተገለጸው ለሰሚው የማይታወቅ የሰው ቋንቋ በልሳን መናገር አለ በሐዋርያት ሥራ እና ላይ በሰማያዊ ቋንቋ የተባሉት አሉ ይህ ሁሉም ክርስቲያን ሊናገርበት የሚገባ ዓይነት ነው ይላሉ እንዲሁም በኛ ቆሮ ላይ ጥቂት ክርስቲያኖች ብቻ ሊናገሩት የሚችሉት ልሳን አለ ይላሉ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ዓይነት ልሳናት ስለመኖራቸው በጭራሽ አይናገርም ቢበዛ ምናልባት ሁለት ዓይነት ልሳናት መኖራቸውን ያመለክት ይሆናል በሐዋርያት ሥራ እንዳለው ሰዎች ፈጽሞ ያልተማሩትን የሰው ቋንቋ በልሳን ለመናገር ችሎታ ይሰጣቸዋል በኛ ቆሮ ላይ ያለው ተናጋሪው ወይም አድማጮቹ ሊረዱት በማይችሉት የመተርጎም ስጦታ ካላቸው ሰዎች በስተቀር የሰው ባልሆነ ቋንቋ በልሳን መናገርም አለ እንደዚሁም ከእግዚአብሔር በስተቀር እነዚህን ልሳናት የሚረዳቸው የለም ነገር ግን በየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ በልሳናት መናገር አንድ ዝም ብሎ የማይቋረጥ የድምጽ ድግግሞሽ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ አንድም ክፍል የለም ልሳናት የሚለው ቃል የሚያመለክተው «ቋንቋዎችን እንጂ ድምፆችን አይደለም ስለዚህ ሰዎች አንድ ዓይነት ድምፅ እየደጋገሙ ሲናገሩ ስንሰማ ይህ አዲስ ኪዳን በልሳናት መናገር ብሎ የሚጠራው እንዳይደለ እርግጠኛ ልንሆን እንችላለን በልሳናት መናገር ሁልጊዜ ተናጋሪው ሊቆጣጠረው የሚችል ነገር ነው በልሳን መናገር ሰመመን ውስጥ ተገብቶ የሚደረግ ነገር አይደለም ኛ ቆሮ በልሳን የሚናገር ሰው በጉባኤው መካከል የእርሱን ልሳን መተርጎም የሚችል ሰው መኖር ያለመኖሩን እስከማወቅ ድረስ ራሱን መቆጣጠር ይችላል ይላል የሚተረጉም ሰው ከሌለ ጸጥ ብሎ በራሱ መንፈስ መጸለይ እስከሚችል ድረስ ራሱን መግዛት ይችላል በልሳናት ስለመናገር የተሰጡ ግልጽና የተወሰኑ መመሪያዎች አሉ በቡድን ወይም በጉባኤ አምልኮ ጊዜ በልሳን የሚናገረው ሰው በቅድሚያ በዚያ የመተርጎም ስጦታ ያለው ሰው መኖር ያለመኖሩን መወስን መቻል አለበት የሚተረጉም ሰው መኖሩን ካረጋገጠ በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ሥልጣን ሥር ሆኖ በልሳናት መናገር ይችላል ነገር ግን የተነገረው ልሳን በአግባቡ መተርጎም ይኖርበታል ይህ ታዲያ አንድ ሰው በልሳን ለረጅም ጊዜ ተናግሮ ተርጓሚው በጥቂት ቃላት የሚተረጉመው ከሆነ ትርጉም ለማለት አያስደፍርም ሐዋርያው ጳውሎስ አጽንኦት ሰጥቶ የሚናገረው በልሳናት የሚናገሩ ሁሉ ተራ በተራ እንዲያደርጉት ነው እንዲሁም በአንድ የአምልኮ ፕሮግራም ላይ የሚተረጉም ካለ ቢበዛ ሦስት ሰዎች ብቻ በልሳናት እንዲናገሩ ነው እነዚህ መመሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ትምህርት ተሰጥቶባቸዋል ስለዚህ አማኞች ግልጽ ትምህርት ለተሰጠባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ራሳቸውን ማስገዛት አለባቸው እንጂ ሌሎች የሚያደርጉትን መከተል የለባቸውም እውነተኛና መንፈሳዊ ለመምሰል ሰይጣን ራሱን እንደ ብርሃን መልአክ ለውጦ ያቀርባል ኛ ቆሮ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የጸፈውን መንፈስ ቅዱስን እየተቃወሙ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ሆነን ነው በልሳን የምንናገረው ብለው ሲያስቡ ሰይጣን በጣም ደስ ይለዋል ኛ ጴጥ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ሕዝቡ ምእመናኑ እግዚአብሔርን ስለ መታዘዙ እርግጠኛ መሆን ይኖርባቸዋል ማለትም በልሳናት የሚናገሩት ሁሉ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ መተርጎም አለባቸው እንዲሁም ሽማግሌዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መንገድ አምልኮውን ለመምራት በሚሞክሩበት ጊዜ አባላት ማዳመጥ ይገባቸዋል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ላይ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ መንቀጥቀጥና እና መጮኽ የመንፈስ ቅዱስ ምልክት ሆኖ አልተጠቀሰም ሁለት ዓይነት የመንፈሳዊ ኃይል ምንጮች መኖራቸውን ማስታወስ ይገባናል አንደኛ ው መንፈስ ቅዱስ ነው ሌላኛው ሰይጣን ነው ሁለቱም ለግለሰቦች ኃይልን ለመስጠትና የሚያስገርሙ ተግባራትን በግለሰቦች ሕይወት ለመፈጸም ፈቃደኞች ናቸው ነገር ግን የሚሠሩበት መንገድ በጣም የተለያየ ነው ሰይጣን ሙሉ በሙሉ ግለሰቡን ተቆጣጥሮ አብዛኛውን ጊዜ የሚሠራው ከሰውየው ፈቃድ ውጭ ነው ለምሳሌ ክፉ መንፈስ የነበረበት ልጅ መንፈሱ መሬት ላይ ጥሎት ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ያንቀጠቅጠው ነበር ማር መንፈስ ቅዱስ ግን ጨዋ ነው በግለሰቡ ሕይወት ውስጥ አገልግሎቱ ለእግዚአብሔር ክብርን እንዲጨምር በማድረግ ነው መንፈስ ቅዱስ ሰውየው የራሱን ድርጊት እስከማይቆጣጠር ድረስ በከፍተኛ ኃይል በፍጹም አይጫንም ጳውሎስ ለዚህ ነው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በልሳናት የሚናገር ወይም የሚተነብይ ስው ያን አገልግሎት ለክርስቶስ አካል ጥቅም በማያመጣ መንገድ እያቀረበ ከሆነ የማቆም አቅም አለው ያለው ኛ ቆሮ መንፈሳዊ ስጦታዎች ምንድን ናቸው።